Onni Niskanen Från Råsunda till Janhoy meda (ኦኒ ኒስካነን፣ ከሮሱንዳ እስከ ጃንሆይ ሜዳ) av Solomon Halefom (ሰሎሞን ሐለፎም)
Denna bok är Onni Niskanens biografi. Onni var en svensk idrottsledare som åkte till Etiopien 1946 och arbetade vid den etiopiske Kejsarens livgarde som idrottsofficer. Framför allt var han tränare till Abebe Bikila, barfotalöparen som segrade i maratonloppet i Rome 1960 och i Tokyo 1964. Dessutom var han också känd på humanitära biståndsverksamhet inom Röda korset, Rädda barnen osv.
አበበ በዚያ ምሽት ሀውልቱን ቀና ብሎ
ሲመለከት ደሙ ፈላ:: ሀውልቱ
በጨለማው መሃል እንደጆቢራ
ተገትሯል:: ቆፍጣናው ወታደር በግፍ
የተጨፈጨፉት ወገኞቹ ታሰቡት::
በባዶ እግራቸው እስከ መጨረሻው
እስትንፋስ ድረስ ለተዋጉት የኢትዮጵያ
አርበኞች ደም መላሽ ሆኖ ፋሽስቱን
የጣሊያን መንግሥት ሊበቀለው
ቆረጠ:: ትንፋሹን አሰባስቦ ፍጥነቱን
ጨመረ:: እስካሁን ድረስ ከጎኑ
እየተከታተለ አላፈናፍን ያለውን ሞገደኛውን የሞሮኮውን ራህዲ ትቶት ወደፊት ሸመጠጠ::
መዳረሻው ላይ ጣሊያን ሰራሹ ድንጋያማው ኦሎምፒያድ ስታዲዮም ባልደፈርም ባይነት
እየራደ ነው:: አበበና የኮንስታንቲን ቅያስ ፊት ለፊት ተፋጠጡ:: የኢትዮጵያን ሕዝብ
አደራ ያነገበው ጥቁሩ አፍሪካዊ ከፊት ለፊቱ ተገትሮ የሚርደውን ግምብ ድጋሚ በዓለም ፊት
ለማዋረድ ፍጥነቱን ጨምሮ በቁርጠኝነት ወደፊት ተፈተለከ።
የመጨረሻውን ክር ሲበጥስ የድካም ስሜት ፈጽሞ አልታየበትም። ሁለት ሰአት ከአስራ አምስት
ደቂቃ ከአስራ ስድስት ሴኮንድ:: አኩሪ ሰዓት:: እየተቅበጠበጠ በጉጉት ሲጠብቅ የነበረው
አሰልጣኙ ኦኒ ኒስካነን በሰዎች መሃል እየተሽሎከሎከ መጥቶ አበበ አንገት ላይ ተጠመጠመ።
ኢትዮጵያዊው አበበ ቢቂላ ለአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ
በአንገቱ ላይ አጠለቀ:: ያገሩ ልጅ አበበ ዋቅጅራም በጣም ብዙ ታዋቂ አትሌቶችን ቀድሞ
በሁለት ሰአት ከሃያ አንድ ደቂቃ ሰባተኛ ሆነ:: ጉሮ ወሸባዬ! ድል ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ
ሆነ።ነጭ አምላኪው አለም ተገረመ፤ አፈረም:: ኢትዮጵያና አፍሪካ ግን አንገታቸውን ቀና
አድርገው በልጃቸው ኮሩ:: አንዳንድ የጣሊያን ጋዜጦችም “ኢትዮጵያን ለመውረር ድፍን
የጣሊያን ሠራዊት ዘመተ:: ጣሊያን ግን በአንድ ቁርጠኛ የኢትዮጵያ ወታደር ተወረረች”
በማለት በበነገታው በፊት ገጾቻቸው ላይ ጻፉ::